የኢትጵያ ሚድዋይፎች ማህበር ለምግብነት የሚውሉ የዛፍ ችግኝ በመትከል “የአረንጓዴ አሻራ” አካሄደ

ለምግብነት የሚውሉ ችግኞችን መትከል ጤናማ ትውልድን ለማፍራት ከማስቻሉም ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንደሚኖራቸው ተገልጿል፡፡ መርሃ ግብሩም “ከኮሮና ቫይረስ እራሳችንን እየጠበቅን የአረንጓዴ አሻራችንን እናሳርፋለን” በሚል መሪ ሃሳብ ተካሂዷል፡፡ ማህበሩ የአረንጓዴ አሻራውን ያሳረፈው “በአራብሳ ጤና ጣቢያ” ቅጥር ግቢ ነው፡፡ በእለቱም እንደ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ ዘይቱን እና ሙዝ ያሉ ለምግብነት የሚውሉ 200 ያህል የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኞች ተተክለዋል፡፡ በማህበሩ አስተባባሪነት ከጤና ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ፣ ከማህበሩ አመራርና አባላት እንዲሁም ከአራብሳ ጤና ጣቢያ የተውጣጡ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

Tags: