የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማህበር የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚረዱ የሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶችን በሶማሊ ክልል ለሚገኙ አምስት የጤና ተቋማት ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማህበር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስችሉ የሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶችን በሶማሊ ክልል ለሚገኙ አምስት የጤና ተቋማት ድጋፍ አድርጓል፡፡ ማኅበሩ ድጋፉን ያደረገው 28ኛው ዓለም አቀፍ የሚድዋይፎች ቀን ምክንያት በማድረግ መሆኑን የገለጹት የማኅበሩ ክትትል፤ ምዘና እና የምርምር ክፍል ኃላፊው አቶ በለጠ በልጉ ናቸው፡፡ ከድጋፉ መካከል 160 ባለአንድ ሊትር ሳኒታይዘር፣ 295 የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎች፣ 24 ለሕክምና ባለሙያዎች የሚያገለግሉ ሙሉ አልባሳት ይገኙበታል።

Tags: